ሰው ወደ ተግባሩ፥ እስኪመሽም ድረስ ወደ ሥራው ይወጣል።
ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤ እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል።
ከዚህ በኋላ ሰዎች ለሥራ ይሰማራሉ፤ እስከሚመሽም ድረስ ሲሠሩ ይውላሉ።
እስራኤልም ወደ ግብፅ ገባ፥ ያዕቆብም በካም ምድር ተቀመጠ።
“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በግንባርህ ላብ እንጀራን ትበላለህ፥ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።”
ከፀሐይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፥ ራስን ለመጉዳት በባለቤቱ ዘንድ የተቀመጠ ሀብት።
የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።
በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።