ጨለማን ታስቀምጣለህ፥ ሌሊትም ይሆናል፥ በእርሱም የዱር አራዊት ሁሉ ይወጡበታል።
ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤ የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ።
አንተ ጨለማን ፈጠርክ፤ ሌሊትም ሆነ፤ በጨለማም የዱር አውሬዎች ሁሉ ይወጣሉ።
ንጉሥ ላከ፥ ፈታውም፥ የሕዝብም አለቃ አድርጎ ሾመው።
በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።”
የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና።
ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፥ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።
ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ አበለጽጋለሁ፤ አደኸያለሁ፤ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ ጌታ ነኝ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ዳርቻቸውን ለማስፋት ሲሉ የገለዓድን እርጉዞች ቀድደዋልና ስለ ሦስት የአሞን ልጆች ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።