ትምህርቴን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸል አትበሉትም።
ምክሬን አድምጡ፤ ጥበበኞች ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት።
የምትማሩትን አስተውሉ፤ ብልኆች ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት።
ጥበብን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸልም አትበሉት።
ግርግር ባለበት አደባባይ ትጣራለች፥ በከተማይቱ መግቢያ በር ቃልን ትናገራለች፦
ጠቢብ እነዚህን በመስማት ዐዋቂነትን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፥
ተግሣጽን ቸል የሚል የራሱን ነፍስ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን አእምሮ ያገኛል።
ምክርን ስማ፥ ተግሣጽንም ተቀበል በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።
ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፥
ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን አድምጥ፥ ጆሮህን ወደ ትምህርቴ አዘንብል፥
የሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላይ ሲያስረዳቸው እምቢ ያሉት ካላመለጡ፥ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ፈቀቅ የምንል እኛ እንዴት እናመልጣለን?