La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 6:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም ምንም ካሣ አይቀበልም፥ ስጦታም ብታበዛለት አይታረቅም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምንም ዐይነት ካሳ አይቀበልም፤ የቱንም ያህል ብዙ ቢሆን መማለጃን ዕሺ አይልም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምንም ዐይነት ካሳ መቀበል አይፈልግም፤ የስጦታም ብዛት ቊጣውን አያበርድለትም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጠብ ካሣ በምንም አይለወጥም፥ በገንዘብ ብዛትም አይታረቀውም።

Ver Capítulo



ምሳሌ 6:35
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቆዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።


እኔም አባቴን የምሰማ ትንሽ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር።


ቅንዓት ለሰው የቁጣ ትኩሳት ነውና፥ በበቀልም ቀን አይራራለትምና።


ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።


ያዘችውም ሳመችውም፥ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦


ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድሁ፥


ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም፥ ፈሳሾችም አያሰጥሙአትም፥ ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል።


እነሆ፤ ለብር ደንታ የሌላቸውን፤ በወርቅም ደስ የማይሰኙትን፤ ሜዶናውያንን አስነሣባቸዋለሁ።


ሰው ዝቅ ብሏል፤ የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል።


ስለዚህ መንገዴን ስላልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።