ምሳሌ 6:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅንዓት ለሰው የቁጣ ትኩሳት ነውና፥ በበቀልም ቀን አይራራለትምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅናት የባልን ቍጣ ይቀሰቅሳልና፤ በሚበቀልበትም ጊዜ ምሕረት አያደርግም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅናት የባልን ቊጣ ያነሣሣል፤ በሚበቀልበትም ጊዜ አይራራም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሏ ቅንዐትንና ቍጣን የተመላ ነውና፥ በፍርድ ቀን አይራራለትም። |
እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፥ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።
“የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በቅንዓቴ በመካከላቸው ቀንቶአልና ቁጣዬን ከእስራኤል ልጆች መለሰ፤ እኔም የእስራኤልን ልጆች በቅንዓቴ አላጠፋሁም።
በባልዋም ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ እርሷም በመርከስዋ ስለ ሚስቱ ቢቀና፤ ወይም እርሷ ሳትረክስ በእርሱ ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፤