ክፉ አሳብን የሚያቅድ ልብ፥ ወደ ክፉ የሚሮጡ እግሮች፥
ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣
ክፉ ሐሳብ የሚያፈልቅ አእምሮ፥ ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚቸኲሉ እግሮች፥
ክፉ ዐሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ክፉዉን ለማድረግ ወዲህና ወዲያ የምትሮጥ እግር፥
ጌታም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ።
የአፉ ቃል ግፍና ሽንገላ ነው፥ ማስተዋልን በጎ ማድረግንም ተወ።
እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።
የበደለኛ አሳብ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ናት፥ ያማረ ቃል ግን ጥሩ ነው።
ልባቸው ግፍን ታስባለችና፥ ከንፈራቸውም ተንኮልን ትናገራለችና።
ክፉ ለማድረግ የሚያውጠነጥን፥ ተንኰለኛ ይባላል።
እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጉስቁልናና ውድመት በሚሄዱበት አለ።
ኢየሩሳሌም ሆይ! እንድትድኚ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?
ክፋትን ለማድረግ በምስጢር ለሚያቅዱና በመኝታቸው ላይ ክፋ ነገርን ለሚሠሩ ወዮላቸው! ሲነጋ ይፈጽሙታል፥ ኃይል በእጃቸው ነውና።
አንዱ በሌላው ላይ ክፉን ነገር በልቡ አያስብ፤ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፤ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል የጌታ ቃል።
“እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤