እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር።
በርሱ ቃል ላይ አንዳች አትጨምር፤ አለዚያ ይዘልፍሃል፤ ሐሰተኛም ያደርግሃል።
እርሱ ያላለውን ብሎአል ብትል ይገሥጽሃል፤ ሐሰተኛ መሆንህንም ይገልጣል።”
ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ፥
ደግሞም እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሞት አስነሥቶታል ብለን በመመስከራችን፥ ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን የማይነሡ ከሆነ፥ ክርስቶስንም አላስነሣውም ማለት ነው፤
“እኔ ያዘዝሁህን ሁሉ ጠብቅ፤ በእርሱ ላይ ምንም አትጨምር፤ ከእርሱም አንዳች ነገር አትቀንስ።”
“ከመካከልህ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ተነሥቶ ምልክት ወይም ድንቅ አደርጋለሁ ቢልህ፥
እኔ ያዘዝኋችሁን የጌታ አምላካችሁን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም።