ምሳሌ 30:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሲኦልና የማትወልድ ማኅፀን፥ ውኃ የማትጠግብ ምድርና፦ “በቃኝ” የማትል እሳት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም መቃብር፣ መካን ማሕፀን፣ ውሃ ጠጥታ የማትረካ ምድር፣ ‘በቃኝ’ የማይል እሳት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም፦ “መቃብር፥ መኻን ሴት፥ ዝናብ የሚያስፈልገው ደረቅ ምድርና ከቊጥጥር ውጪ የሆነ የእሳት ቃጠሎ” ናቸው። |
በእርግጥ ወይን አታላይ ነው፤ ትዕቢተኛ ሰው በስፍራው አርፎ አይቀመጥም፤ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፤ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።