ምሳሌ 3:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፥ ሞኞች ግን መዋረድን ይቀበላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤ ሞኞችን ግን ለውርደት ያጋልጣቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠቢባን መልካም ክብርን ያገኛሉ፤ ሞኞች ግን ውርደትን ይከናነባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤ ሰነፎች ግን ውርደታቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።