ጌታ መታመኛህ ይሆናልና፥ እግርህም እንዳይጠመድ ይጠብቅሃልና።
እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፤ እግርህንም በወጥመድ ከመያዝ ይጠብቃል።
እግዚአብሔር መታመኛህ ሆኖ በወጥመድም ከመያዝ ይጠብቅሃል።
እግዚአብሔር በመንገድህ ሁሉ ይኖራልና፥ እግሮችህም እንዳይነዋወጡ ያቆማቸዋልና።
አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?
እግርህ እንዲናወጥ አይፈቅድም፥ የሚጠብቅህም አይተኛም።
እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።
ጌታን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል።
እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።