ምሳሌ 29:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ በፍትሕ አገሩን ያጸናል፥ ጥቅም የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍትሕን በማስፈን ንጉሥ አገርን ያረጋጋል፤ ጕቦ ለማግኘት የሚጐመጅ ግን ያፈራርሳታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ፍትሕ እንዳይጓደል በሚያደርግበት ጊዜ ሀገሩን ያረጋጋል፤ ሕዝብን የሚበዘብዝ መሪ ግን ሀገሩን ወደ ጥፋት ያደርሳል። |
በአምላክህ በጌታ ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ሊያስቀምጥህ የወደደህ አምላክህ ጌታ ብሩክ ይሁን፤ አምላክህ እስራኤልን ለዘለዓለም ሊያጸናቸው ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድና ጽድቅ እንድታደርግ በእነርሱ ላይ አነገሠህ።”
“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፥ ምድርንም እንድታቀና፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች እንድታወርስ፥
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “የማይገባህን አደረግህ፤ አምላክህ ጌታ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፤ ዛሬ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ባጸናልህ ነበር፤