ክፉዎች በተነሡ ጊዜ ሰዎች ይሸሸጋሉ፥ እነርሱ በጠፉ ጊዜ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።
ክፉዎች ሥልጣን በሚይዙ ጊዜ ሕዝብ ይሸሸጋል፤ ክፉዎች በሚጠፉበት ጊዜ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።
ክፉ ሰዎች ሲሾሙ ሰዎች ይደበቃሉ፤ እነርሱ ሲሻሩ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።
በእነርሱም ዘንድ ተሸሽጎ በጌታ ቤት ስድስት ዓመት ያህል ተቀመጠ፤ ጎቶልያም በምድሪቱ ላይ ነገሠች።
ድሆቹን ከመንገድ ያስወጣሉ፥ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ይሸሸጋሉ።
ጻድቃን ድል ባደረጉ ጊዜ ብዙ ክብር አለ፥ ክፉዎች ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ ግን ሰው ይሸሸጋል።
ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፥ በድሆች ላይ ዐይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል።
ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።
ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፥ ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።