ወንድሜን ሐናኒንና የምሽጉ አዛዥ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ኀላፊነት ሰጠኋቸው፤ እርሱም እውነተኛና ከሌሎች ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
ምሳሌ 28:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፥ ሀብታም ለመሆን የሚቸኩል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታማኝ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ከቅጣት አያመልጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታማኝ ሰው የተባረከ ሕይወት ይኖረዋል፤ ሀብታም ለመሆን የሚስገበገብ ሰው ግን ቅጣት ያገኘዋል። |
ወንድሜን ሐናኒንና የምሽጉ አዛዥ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ኀላፊነት ሰጠኋቸው፤ እርሱም እውነተኛና ከሌሎች ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “መጋቢ የሚያገለግለው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፤ ‘ይህ ሰው ያለህን ይበትናል፤’ የሚል ክስ በእርሱ ዘንድ አቀረቡ።
የሚጠብቅህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያስገባ ነው፤ ለዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።
“የት እንደምትኖር አውቃለሁ፥ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ነው፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።
አቢሜሌክም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “የንጉሥ ዐማች፥ የክብር ዘቦችህ አዛዥና በቤተሰብህ ዘንድ እጅግ የተከበረው ዳዊትን የመሰለ ታማኝ ከአገልጋዮችህ ሁሉ ማን አለ?