ደግሞስ ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን?
ምሳሌ 28:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቃን ድል ባደረጉ ጊዜ ብዙ ክብር አለ፥ ክፉዎች ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ ግን ሰው ይሸሸጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን ድል ሲነሡ ታላቅ ደስታ ይሆናል፤ ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ይሸሸጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች ድል በሚያደርጉበት ጊዜ ሰው ሁሉ ይደሰታል፤ ክፉ ሰዎች ሥልጣን በሚይዙበት ጊዜ ግን ሰው ሁሉ በሐዘን አንገቱን ይደፋል። |
ደግሞስ ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን?
በሰባተኛውም ወር በሃያ ሦስተኛውም ቀን ሕዝቡን ወደ ድንኳናቸው አሰናበተ፤ ጌታ ለዳዊትና ለሰሎሞን ለሕዝቡም ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ደስ ብሎአቸው ሐሴትን እያደረጉ ሄዱ።
ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን እንዲይዙ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፥ ጌታ ግን ሰወራቸው።
በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።
በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ ጌታ አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደጣለህ እነሆ በገዛ ዓይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፥ ‘ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።