ምሳሌ 28:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብታም ሰው ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል፥ አስተዋይ ድሀ ግን ይመረምረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለጠጋ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥር ይሆናል፤ አስተዋይ የሆነ ድኻ ግን መርምሮ ያውቀዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታም ሰው ዘወትር ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል፤ አስተዋይ የሆነ ድኻ ግን የእርሱን ጠባይ መርምሮ ያውቃል። |
ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።