ምሳሌ 28:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚያስት፥ እርሱ ወደ ጉድጓዱ ይወድቃል፥ ፍጹማን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚመራ፣ በቈፈረው ጕድጓድ ይገባል፤ ንጹሓን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነተኛውን ሰው አግባብቶ ወደ ክፉ መንገድ የሚመራ ባጠመደው ወጥመድ ይያዛል፤ ንጹሕ ሰው ግን የመልካም ሥራውን ዋጋ ያገኛል። |
ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበለዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር አሉና።
አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና።