La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 27:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የወዳጅ ማቁሰል ለክፉ አይሰጥም፥ የጠላት መሳም ግን የውሸት ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣ የወዳጅ ማቍሰል ይታመናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የወዳጅ ማቊሰል ለመልካም ነገር ነው፤ የጠላት መሳም ግን ለጥፋት ነው።

Ver Capítulo



ምሳሌ 27:6
12 Referencias Cruzadas  

ጻድቅ በጽኑ ፍቅር ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የክፉ ሰው ዘይት ግን ራሴን አይቀባ፥ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና።


ጥላቻን የሚከድን ሐሰተኛ ከንፈር አለው፥ ሐሜትንም የሚገልጥ አላዋቂ ነው።


የሰንበር ቁስል ክፉዎችን ያነጻል፥ ግርፋትም ወደ ሆድ ጉርጆች ይገባል።


የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፥ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር እንኳ ጣፋጭ ነው።


በምላሱ ከሚሸነግል ይልቅ ሰውን የሚገሥጽ በኋላ ሞገስ ያገኛል።


እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበር፤ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።