6 የወዳጅ ማቊሰል ለመልካም ነገር ነው፤ የጠላት መሳም ግን ለጥፋት ነው።
6 ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣ የወዳጅ ማቍሰል ይታመናል።
6 የወዳጅ ማቁሰል ለክፉ አይሰጥም፥ የጠላት መሳም ግን የውሸት ነው።
ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።
ጥላቻውን የሚሸፍን ሰው ሐሰተኛ ነው፤ ሐሜትንም የሚያሠራጭ ሰው ሞኝ ነው።
የሚያቈስል ቅጣት ክፉ ነገርን ያስወግዳል፤ ግርፋትም የሰውን ውስጣዊ ሁኔታ ያነጻል።
የጠገበ ሰው ማር. አይጥመውም፤ የራበው ሰው ግን መራራው ነገር እንኳ ይጣፍጠዋል።
ሰውን ከማቈላመጥ ይልቅ እየመከረ የሚገሥጸውን ሰው በመጨረሻ ያመሰግነዋል።
እነርሱ መልካም መስሎ እንደ ታያቸው ለጥቂት ጊዜ ቀጥተውናል፤ እርሱ ግን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ይቀጣናል።
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤