ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለሴት አገልጋዮችህ ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል።
አንተንና ቤተ ሰብህን፣ ገረዶችህንም ጭምር ለመመገብ፣ የተትረፈረፈ የፍየል ወተት ይኖርሃል።
የቀሩት ፍየሎች ለአንተና ለቤተሰብህ ለሴት አገልጋዮችህም ጭምር የሚጠቅም ወተት ይሰጡሃል።
በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ።
ክፉ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፥ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ተማምኖ ይኖራል።
መብሏን በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች።
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፥ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።