ውኃ ፊትን እንደሚያሳይ፥ እንዲሁ የሰው ልብ ለሰው ይታያል።
ውሃ ፊትን እንደሚያሳይ፣ የሰውም ልብ ማንነቱን ገልጾ ያሳያል።
ውሃ እንደ መስተዋት ሆኖ ፊትህን እንደሚያሳይህ ኅሊናህም እንደ መስተዋት ሆኖ የራስህን ጠባይ መልሶ ያሳይሃል።
ጌታም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ።
እርሱ ብቻውን ልባቸውን የሠራ ሥራቸውንም ሁሉ የሚያስተውል።
በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።
ሲኦልና ጥፋት እንደማይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዐይን አይጠግብም።
ከውስጥ፥ ከሰው ልብ የሚወጡት ክፉ ሐሳብ፥ ምንዝር፥ ስርቆት፤ ሰው መግደል፥ ዝሙት፥