La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 26:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ አትመልስለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሞኝን እንደ ቂልነቱ አትመልስለት፤ አለዚያ አንተም ራስህ እንደ እርሱ ትሆናለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የማይረባ ጥያቄ ለሚያቀርብልህ ሞኝ ሰው፥ አንተም እንደ እርሱ ሞኝ እንዳትሆን መልስ አትስጠው።

Ver Capítulo



ምሳሌ 26:4
14 Referencias Cruzadas  

ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት “አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!” ሲል መለሰላቸው።


ሕዝቡ፥ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ “ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ከዳዊት ጋር ምን ርስት አለን፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየድኳንኖችህ ሂድ! ዳዊት ሆይ የራስህን ቤት ጠብቅ!” ብለው መለሱለት። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ።


የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።


በሞኝ ጆሮ ምንም አትናገር፥ በቃልህ ጥበብ ያፌዛልና።


ለራሱ ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት።


ጠቢብ ከሞኝ ጋር ቢጣላ፥ ሞኙ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ዕረፍትም አይኖርም።


እነርሱ ግን ዝም አሉ፥ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና “አንዳችም አልመለሱለትም”።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም በረከትን ልትወርሱ ተጠርታችኋል።


ነገር ግን የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ሲናገር “ጌታ ይገሥጽህ!” አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊያመጣበት አልደፈረም።