ሐሰተኛ ምላስ ያቈሰላቸውን ሰዎች ይጠላል፥ ልዝብ አፍም ጥፋትን ያመጣል።
ሐሰተኛ ምላስ የጐዳቻቸውን ትጠላለች፤ ሸንጋይ አንደበትም ጥፋትን ታመጣለች።
ዋሾ አንደበት የሚጐዳቸውን ሰዎች ይጠላል፤ የሽንገላ ንግግርም ጥፋትን ያመጣል።
ታሪኩንም እንዲህ ስትል ነገረችው፤ “አንተ ያመጣኸው ዕብራዊ ባርያ መሣቂያ ሊያደርገን ወዳለሁበት ሰተት ብሎ ገባ፤
ከእንግዳይቱ ሴት አንተን ለመታደግ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከማትታወቀው ሴት፥
ወዳጁን በሽንገላ የሚናገር ሰው ለእግሩ ወጥመድን ይዘረጋል።
ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ ከሌላይቱም ሴት አታላይ ምላስ።
ከአምንዝራ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፥ ቃሏን ካለዘበች ከሌላይቱ ሴት።
ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የምነገራችሁን እኔን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።