La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 26:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንዲያበዛ፥ እንዲሁ ቁጡ ሰው ጠብን ያበዛል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሰል ፍምን፣ ዕንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ አዋኪ ሰውም ጠብን ያባብሳል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሰል ፍምን፥ እንጨትም እሳትን እንደሚያበዛ ጠብ አጫሪ ሰው ጠብን ያባብሳል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 26:21
8 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”


እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባኤአቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረም የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር።


እንደ በረሃ እንጨት ፍም የኃያላን ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።


ጥላቻ ክርክርን ታስነሣለች፥ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ትከድናለች።


ቁጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፥ ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል።


ቁጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል። ወፈፍተኛ ሰውም ኃጢአትን ያበዛል።


ወተት መናጥ ቅቤን ያወጣል፥ አፍንጫንም መጭመቅ ደምን ያወጣል፥ እንዲሁም ቁጣን መጐተት ጠብን ያመጣል።