በማይመለከተው ገብቶ የሚሟገት፥ ውሻን በጆሮው እንደሚይዝ ነው።
በሌሎች ጠብ ጥልቅ የሚል መንገደኛ፣ የውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው።
በማይመለከትህ ነገር መከራከር በመንገድ የሚተላለፈውን የውሻ ጆሮ እንደ መያዝ ይቈጠራል።
ክፉ ሰው ዓመፃን ብቻ ይሻል፥ ስለዚህ ጨካኝ መልአክ ይላክበታል።
የሰነፍ ከንፈር በጥል ውስጥ ትገባለች፥ አፉም በትርን ትጠራለች።
ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።
ትንታግንና ፍላጻን ሞትንም እንደሚወረውር እንደ ዕብድ ሰው፥
እርሱ ክፉ ካልሠራብህ፥ ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ።
እርሱም “አንተ ሰው! ለዳኝነትና ለማከፋፈል ማን ነው በላያችሁ የሾመኝ?” አለው።