ሙግትህን ከባልንጀራህ ጋር በቀጥታ ፈጽም፥ የሌላ ሰው ምሥጢር ግን አትግለጥ፥
ስለ ራስህ ጕዳይ ከባልንጀራህ ጋራ በምትከራከርበት ጊዜ፣ የሌላውን ሰው ምስጢር አታውጣ፤
በአንተና በባልንጀራህ መካከል ክርክር ቢነሣ ከእርሱ ጋር ተወያይተህ አለመግባባትህን አስወግድ እንጂ የሌላን ሰው ምሥጢር አታውጣ።
ለሐሜት የሚሄድ ምሥጢሩን ይገልጣል፥ በመንፈስ የታመነ ግን ነገሩን ይሰውራል።
ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ሰውን አትገናኘው።
የሚሰማ እንዳይነቅፍህ፥ ስምህንም ለሁልጊዜ እንዳያጠፋው፤