ምሳሌ 25:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትዕግሥት አለቃ ይለዝባል፥ ገር ምላስ አጥንትን ይሰብራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በትዕግሥት ገዥን ማግባባት ይቻላል፤ ለስላሳ አንደበትም ዐጥንት ይሰብራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትዕግሥት ማግባባት ታላቅ ተቃውሞን ያበርዳል፤ መሪዎችን ሳይቀር በሐሳብ እንዲስማሙ ያደርጋል። |
በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።
ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢጌል እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ዳዊት ሰላምታውን እንዲያቀርቡለት ከምድረበዳ ወደ ጌታችን መልእክተኞች ልኮ ነበር፤ እርሱ ግን በስድብ አዋረዳቸው።