ምሳሌ 23:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፥ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁልጊዜ ስለ ዋጋ የሚያሰላ ሰው ነውና፤ “ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ ልቡ ግን ከአንተ ጋራ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከልቡ ሳይሆን ምግቡን እንድትተውለት ፈልጎ ለማስመሰል ያኽል “ብላ፥ ጠጣ” ይልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣርን እንደሚበላ ይበላል፥ ይጠጣልም፤ ወደ አንተም አታስገባው፥ ከእርሱ ጋርም እንጀራን አትብላ፥ ብላ፥ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም። |
የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና፤” ሲል በልቡ አሰበ።
ከዚያም፥ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኃይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።