ምሳሌ 23:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሌባ ታደባለች የእምነተቢሶችንም ቍጥር ታበዛለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ወንበዴ ታደባለች፤ በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ወንበዴ አድብተው ይጠብቁሃል፤ ብዙ ወንዶችን በሕጋዊ ጋብቻ ታማኝ ሆነው እንዳይኖሩ አድርገዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሷ የሄደ ፈጥኖ ይጠፋል፥ ጠማማ ሰውም ሁሉ ያልቃል። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ወደ ተራቈቱ ኮረብቶች አይኖችሽን አንሺ፥ ተመልከቺም፤ ያልተጋደምሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ልክ በምድረ በዳ እንደሚቀመጥ አረባዊ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ ትጠብቂያቸዋለሽ፤ በግልሙትናሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።