ምሳሌ 23:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይውደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ ልብህን ስጠኝ፤ ዐይኖችህም ከመንገዴ አይውጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ፥ በጥንቃቄ አድምጠኝ፤ የእኔ አኗኗር ምሳሌ ይሁንህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይጠብቁ። |
ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።
“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።