ምሳሌ 23:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነትን ገንዘብህ አድርግ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም ግዛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ገንዘብህ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነትን፥ ጥበብን፥ ተግሣጽን፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጋቸው እንጂ አትተዋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነትን ግዛ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብንና ተግሣጽን፥ ማስተዋልንም። |
“መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው በእርሻ ውስጥ አግኝቶ መልሶ የሸሸገው የተሰወረ መዝገብ ትመስላለች፤ ከደስታውም ብዛት ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ያንን እርሻ ገዛው።
ሀብታም እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ የምትጐናጸፈውን ነጭ ልብስ፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳልበትን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።