የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
የወለደህን አባትህን አድምጥ፤ እናትህንም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
የወለደህ እርሱ ስለ ሆነ የአባትህን ምክር ስማ፤ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
ልጄ ሆይ፥ የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፥
ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፥ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ይንቃል።
አባቱን የሚረግም፥ እናቱንም የማያመሰግን ትውልድ አለ።
በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዐይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል።
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ትምህርት አትተው፥
ከእናንተ እያንዳንዱ ሰው እናቱንና አባቱን ያክብር፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ፥ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
“በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።
ሙሴ፥ አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ፈጽሞ ይሙት ብሎ ነበርና፤
“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።