በበትር ትመታዋለህ፥ ነፍሱንም ታድናለህ።
በአርጩሜ ቅጣው፤ ነፍሱንም ከሞት አድናት።
እንዲያውም በአርጩሜ ብትመታው ሕይወቱን ከሞት ለማዳን ጥሩ ዋስትና ይሆነዋል።
አንተ በበትር ትመታቸዋለህ፥ ነፍሳቸውን ግን ከሞት ታድናለህ።
በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፥ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።
ቂልነት በልጅ ልብ ውስጥ ተተብትቧል፥ የተግሣጽ በትር ግን ነፃ ያደርገዋል።
ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።
እንደዚህ ያለው ሰው፥ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን እንድትድን፥ ሥጋው ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት።