የልብን ንጽሕናን የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
የልብ ንጽሕናን ለሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
የልብ ንጽሕናንና መልካም ንግግርን የሚወድ ሰው በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ይሆናል።
እግዚአብሔር የልብን የውሀት ይወድዳል። ንጹሓንም ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተመረጡ ናቸው። ንጉሥ በከንፈሩ ይገዛል።
ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ።
ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።
እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ በሽንገላ ያልማለ።
ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፥ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።
አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል፥ በሚያሳፍር ላይ ግን ቁጣው ይሆናል።
የጽድቅ ከንፈር የነገሥታት ደስታ ናት፥ በቅን የሚናገር እርሱንም ይወድዱታል።
የጌታ ዐይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፥ የአታላዩን ቃላት ግን ይገለብጣል።
የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፥ የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፤ ከአፉም ከሚወጡት ቃላት ጸጋ የተነሣ እየተደነቁ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።