ምሳሌ 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው፥ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ልብ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ሐሳብ በጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ እንዳለ ውሃ ነው፤ ይሁን እንጂ ማስተዋል ያለው ሰው ይቀዳዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምክር በሰው ልብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል። |
በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር የሰውን ነገር የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን ነገር ማንም አያውቅም።