ምሳሌ 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እርሷ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ወደ ሕይወት ጎዳናም አይደርሱም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እርሷ የሚገባ ማንም አይመለስም፤ የሕይወትንም መንገድ አያገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርስዋ የሚሄድ ሁሉ አይመለስም፤ የሕይወትንም ጐዳና ማግኘት አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ቀና መንገዶችንም አያገኙም፥ ሕይወት በአለው ዘመንም አይገኙም። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ወንዶችም ደግሞ ከአመንዝሮች ጋር አብረው ይሄዳሉና፥ በአማልክቶቻቸውም መቅደስ ከሚያመነዝሩ ሴቶች ጋር ይሠዋሉና ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማዊ በሆኑ ጊዜ፥ ምራቶቻችሁም ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም፤ የማያስተውልም ሕዝብ ይጠፋል።
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።