ምሳሌ 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብን የሚያገኝ ነፍሱን ይወድዳል፥ ማስተዋልንም የሚጠብቅ መልካም ነገርን ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብን ገንዘቡ የሚያደርጋት ነፍሱን ይወድዳል፤ ማስተዋልን የሚወድዳት ይሳካለታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብን የሚገበይ ሰው ራሱን ይወዳል፤ ዕውቀትን አጥብቆ የሚይዝ ይበለጽጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብን የሚያገኝ ራሱን ይወድዳል፥ ማስተዋልንም የሚጠብቅ መልካም ነገርን ያገኛል። |
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”