ታካች ሰው እጁን በወጭቱ ያጠልቃታል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።
ሰነፍ እጁን ወጭት ውስጥ ያጠልቃል፤ ወደ አፉ ግን መመለስ እንኳ ይሳነዋል።
አንዳንድ ሰዎች በጣም ሰነፎች ናቸው፤ ሌላው ቀርቶ በወጥ ያጠቀሱትን እንጀራ መጒረስ ይታክታቸዋል።
ታካች ሰው እጁን በብብቱ ይሸሽጋል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።
እጅህንም ለምን ትመልሳለህ? ቀኝ እጅህንም ለምን በብብትህ መካከል ታቆያለህ?
ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።
የታካች መንገድ እንደ እሾህ አጥር ናት፥ የጻድቃን መንገድ ግን የተደላደለች ናት።
ሥራ መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች።
ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ከእኔ ጋር እጁን በሳሕኑ ውስጥ የሚያጠልቀው፥ እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል።
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ፥ ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ውስጥ የሚያጠልቀው ነው።