ሥራ መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች።
ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ ዋልጌም ሰው ይራባል።
ስንፍና እንቅልፍን ያስከትላል፤ ስለዚህም ሰነፍ ሰው ይራባል።
ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።
በሥራው ታካች የሚሆን የሀብት አጥፊ ወንድም ነው።
ታካች ሰው እጁን በወጭቱ ያጠልቃታል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።
ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፥ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።
ሰነፍ ሰው፦ “ውጪ አንበሳ አለ፤ ብወጣ፥ በመንገዱ ላይ እሞታለሁ” ይላል።
ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉና፥ የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና።
ትንሽ መተኛት፥ ትንሽ ማንቀላፋት፥ ለማረፍ እጅህን ታጥፋለህ፥
የቤትዋንም ሰዎች አካሄድ በደኅና ትመለከታለች፥ የሀኬትንም እንጀራ አትበላም።
እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
ጉበኞቹ ዕውሮች ናቸው፥ ሁሉም እውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።
የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ስለዚህ “አንተ የምታንቀላፋ ንቃ፤ ከሙታንም ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል፤” ተብሏል።
እንዲሁም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ማንም ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበር።