የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፥ ከንፈሩም ከሚያፈራው ይጠግባል።
ሰው በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤ በከንፈሩም ምርት ይረካል።
ሰው በሚናገረው የንግግር ውጤት በመርካት ተደስቶ ይኖራል።
ሰው ሆዱን ከአፉ ፍሬ ይሞላል፥ ከከንፈሩም ፍሬ ይጠግባል።
ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል፥ የዓመፀኞች ነፍስ ግን ግፍን ትሻለች።
ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ።
የተበደለ ወንድም እንደ ጸናች ከተማ ጽኑ ነው፥ ክርክራቸውም እንደ ግንብ ብረት ነው።
እነርሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ አስደሳች ነገር ይሆንልሃልና።