ወደ ፍርድ አስቀድሞ የገባ ጻድቅ ይመስላል፥ ባልንጀራው ግን መጥቶ ይመረምረዋል።
አስቀድሞ ጕዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው።
በአደባባይ በመጀመሪያ ቀርቦ የሚናገር ሰው ተከራካሪው መጥቶ ጥያቄ እስከሚያቀርብለት ድረስ፥ ዘወትር እርሱ ብቻ ትክክል የሆነ ይመስለዋል።
ከፍርድ በፊት ራሱን የሚከስስ ጻድቅ ነው፥ ያመጣው ባላጋራውም ይገሠጻል።
ጌታውም “ባርያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ፥ ተቈጣ።
ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።
የሰው ስጦታ መንገዱን ታሰፋለታለች፥ በታላላቆችም ፊት ታገባዋለች።
ዕጣ ክርክርን ትከለክላለች፥ በኃያላንም መካከል ትበይናለች።