ምሳሌ 16:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግፍን መሥራት በንጉሥ ዘንድ ጸያፍ ነገር ነው፥ ዙፋን በጽድቅ ይጸናልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፋትን ማድረግ ለነገሥታት አስጸያፊ ነው፤ ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንግሥት የሚጸናው በፍትሕ ስለ ሆነ ክፉ ሥራ በመሪዎች ዘንድ የተጠላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉን የሚሠራም በንጉሥ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የፍርድ ዙፋን በጽድቅ ይጸናልና። |
ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።