ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።
ምሳሌ 15:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቡ የሚያዝን ሰው ዘመኑ ሁሉ የከፋች ናት፥ የልብ ደስታ ግን ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተጨቈኑ ሰዎች ዘመናቸው ሁሉ የከፋ ነው፤ በደስታ የተሞላ ልብ ግን የማይቋረጥ ፈንጠዝያ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጭቊን ኑሮ ዘወትር ጐስቋላ ነው፤ ደስተኞች ሰዎች ግን ዘወትር በኑሮአቸው ይረካሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክፉዎች ዐይኖች ሁልጊዜ ክፋትን ይመለከታሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ሁልጊዜ ዝም ይላሉ። |
ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።
ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።
ይልቅስ የእርሱ ክብር በሚገለጥበት ጊዜ ደግሞ ደስ ብሎአችሁ ኀሤት እንድታደርጉ የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በሆናችሁበት መጠን ደስ ይበላችሁ።