ምሳሌ 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ መቅሠፍት መንገድን በተወ ሰው ላይ ይመጣል፥ ዘለፋንም የሚጠላ ይሞታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመንገድ የሚወጣ ሰው ጥብቅ ቅጣት ይጠብቀዋል፤ ዕርምትን የሚጠላ ይሞታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክለኛውን መንገድ ትቶ ስሕተት የሆነ ነገር የሚያደርግ ይቀጣል፤ ተግሣጽንም የሚጠላ ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅኖች ትምህርት በሚያልፉ ሰዎች ትታወቃለች። ተግሣጽን የሚጠሉ ግን በውርደት ይሞታሉ። |
ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ በፈረሱ አመለጠ።
አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ሰው ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።