ምሳሌ 14:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፥ ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለፍተው የሠሩት ሁሉ ትርፍ ያስገኛል፤ ከንቱ ወሬ ግን ወደ ድኽነት ያመራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተግቶ መሥራት ጥቅምን ያስገኛል፤ ወሬኛነት ግን ያደኸያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁሉ ነገር ጠንቃቃ ለሆነ ብዙ ትርፍ አለው። ደስታን ፈላጊና ሰነፍ ግን ችግረኛ ነው። |
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።