ምሳሌ 13:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም እውቀት ሞገስን ይሰጣል፥ የወስላቶች መንገድ ግን ሸካራ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ማስተዋል ሞገስን ታስገኛለች፤ የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ መሆን ያስከብራል፤ ከዳተኛነት ግን ወደ ጥፋት ያደርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካም ዕውቀት ሞገስንና ጥበብን ይሰጣል፤ የቸለልተኞች መንገድ ግን በጥፋት ውስጥ ነው። |
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።