ምሳሌ 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጁን የሚንቅ ልበ ጐደሎ ነው፥ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልበ ቢስ ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤ አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንቀት ተናግሮ ሰውን የሚያዋርድ፥ ማስተዋል የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል። |
ከዚያም ዜቡል፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜልክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልካቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው።
አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች ግን፥ “እንዲህ ያለ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል?” በማለት ናቁት፤ ስጦታም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።