የሐሰት ሚዛን በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው፥ እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።
እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሠኘዋል።
እግዚአብሔር በሐሰተኛ ሚዛን የሚያታልሉትን ሰዎች ይጠላል፤ በትክክለኛ ሚዛን በሚመዝኑት ሰዎች ግን ይደሰታል።
አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው።
እውነተኛ ሚዛንና መመዘኛ የጌታ ናቸው፥ የከረጢት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ሥራ ናቸው።
ሁለት ዓይነት ሚዛንና ሁለት ዓይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በጌታ ፊት ርኩሳን ናቸው።
ሁለት ዓይነት ሚዛን በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም።
“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።”
ከከነዓን ወገን ነው፤ በእጁ የተንኰል ሚዛን አለ፥ ሽንገላንም ይወድዳል።