ምሳሌ 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሀብታም መዝገቡ የጸናች ከተማ ናት፥ የድሆች ውድቀት ድህነታቸው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለጸጋን ሀብቱ እንደ ምሽግ ሆኖ ይጠብቀዋል፤ ድኻውን ግን ድኽነቱ ያጠፋዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባለጠጋ ሀብት የጸናች ከተማ ናት፤ የዕውቀት ድህነት ግን የኀጢአተኞች ጥፋት ነው። |
ደቀ መዛሙርቱም በንግግሩ ተገረሙ፤ ኢየሱስ ግን እንደገና መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ልጆች ሆይ፤ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ከባድ ነገር ነው፤
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።