ምሳሌ 1:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክሬን ሁሉ ግን ችላ ስላላችሁ፥ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክሬን ሁሉ ስለ ናቃችሁ፣ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምክሬን ናቃችሁ፤ ተግሣጼንም አልተቀበላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምክሬን ሁሉ ናቃችሁ፥ ዘለፋዬንም አልተመለከታችሁም፥ |
እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሆነ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፥ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና በእነርሱ ላይ የተናገርኩትን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በተቀመጡ ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።”