La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 4:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌድሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፥ ሸክማቸውም ሁሉ፥ ሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በየአገልግሎታቸውም የሚደርስባቸውን ሸክም ሁሉ ለእያንዳንዳቸው ትደለድላላችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጌርሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፣ ሸክምም ሆነ ሌላ ሥራ አሮንና ልጆቹ በሚሰጡት አመራር መሠረት ይሆናል። የሚሸከሙትን ሁሉ በኀላፊነት ታስረክቧቸዋላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሚሸከሙአቸው ነገሮችና በሚሠሩአቸው ሥራዎች የጌርሾንን ልጆች አገልግሎት አሮንና ልጆቹ ይቈጣጠሩአቸዋል፤ መሸከም ያለባቸውንም ነገሮች ሁሉ ትመድብላቸዋለህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ፥ በተ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ፥ በሥ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ትእ​ዛዝ ይሁን፤ በስ​ማ​ቸ​ውና በተ​ራ​ቸ​ውም ትቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጌድሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፥ ሸክማቸውም ሁሉ፥ ሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ የሚደርስባቸውንም ሸክም ሁሉ ትነግሩአቸዋላችሁ።

Ver Capítulo



ዘኍል 4:27
4 Referencias Cruzadas  

የአደባባዩንም መጋረጆች፥ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መግብያ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ የሚገለገሉባቸውንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ እነርሱንም በሚመለከት ሊደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ያድርጋሉ።


የጌድሶናውያን ወገኖች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ሥራቸውንም የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታማር ይቈጣጠራል።


ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፤


ወንድሞች ሆይ! በሁሉ ስለምታስቡኝና እኔ ያስተላለፍኩላችሁን ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።